በለስ ብጋብዝህ ተቀብለህ በላህ፣
ከዚያም አውቀህ አፈርክ፣መራቆቱን ገላህ።
እርቃኔን አይቼ እኔም በማፈሬ፣
ሀፍረቴን ልሸፍን በድብዳብ አስሬ፣
ከገነት ተባርረን ስንኖር በምድር፣
በላብ በወዛችን ጥረን ስናድር፣
"በአምላክ ግቢ እንዳልኖር በአጥር በክልሉ፣

ምክንያቴ ናት" ብለህ ታማኛለህአሉ።
ኧረ ለመሆኑ፤
ሰይጣን ከአምላክ ግቢ ሊያስወጣን አስቦ፣
ሊያስተን ሲመጣ በሆዱ ተስቦ፣
ለምን አንተን ተወህ?
ምን ፈለገ ከእኔ?
በመታለሌ እንጂ የዋህ በመሆኔ።
እኔን አልፎ አንተን ሊያስት ግንቢያስብ፣
ትረዳበታለህ የልቡን አሳብ ፣
ይነቃቃልና እባብ ለ እባብ።